• ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ወቅታዊ ጉዳዮች
  • ቪድዮና ድምጾች
  • መጣጥፎች
  • ማህደር
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • LIVE
  • Language
    • ትግርኛ
    • English
አትራኖስ ሚድያ
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ወቅታዊ ጉዳዮች
  • ቪድዮና ድምጾች
  • መጣጥፎች
  • ማህደር
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • LIVE
  • Language
    • ትግርኛ
    • English
አትራኖስ ሚድያ
Home » አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ
መጣጥፍ

አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ

July 6, 2021Updated:September 16, 2021No Comments3 Mins Read

ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ከዚህ ቀደም ከነበሩት የላቁ ናቸው የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችንና አዲስ አይፓድ አስተዋወቀ።

በዚህም አፕል አራት ስልኮችን ያስተዋወቀ ሲሆን እነሱም አይፎን 13 ሚኒ፣ አይፎን 13፣ አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ የተባሉ ናቸው።

አይፎን 13 ፕሮ እና አይፎን 13 ፕሮ ማክስ ከጀርባቸው ሦስት ካሜራዎች ተገጥመውላቸዋል። አፕል ካሜራዎቹ “እጅጉን የረቀቁ የካሜራ ሥርዓት ናቸው” ብሏል።

አፕል ያስተዋወቃቸው አዲሶቹ አይፎን 13 ስልኮች ይዘው ከመጡት ገጽታዎች [ፊቸሮች] መካከል የበርካቶችን ቀልብ የሳበው፤ ‘በፖርትሬይት ሞድ’ ቪዲዮ መቅረጻቸው ነው።

ከዚህ ቀደም ከአይፎን 7 ወዲህ ያሉ የአፕል ስልኮች በፖርትሬይት ሞድ ፎቶ ማንሳት እንጂ ቪዲዮ መቅረጽ አያስችሉም ነበር።

ፖርትሬይት ሞድ ለምሳሌ አንድን ሰው ከጀርባው ያለውን ዳራ በማደብዘዝ ፎቶ በሚነሳው ሰው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ቀልብ መሳብ የሚችል ምስል ማንሳት ያስችላል።

አይፎን 13 ደግሞ ይህን ወደ ቪዲዮ ከፍ አድርጎታል። የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ እንደሚሉት ከሆነ ተጠቃሚዎች በፕሮትሬይት ሞድ ቪዲዮ ከቀረጹ በኋላ ኤዲት ማድረግ የሚያስችለው አይፎን-13 ስልክ ብቻ ነው ይላሉ።

ከዚህ በተጨማሪ አዳዲሶቹ አይፎን ስልኮች ተግባራትን በፍጥነት መከወን የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።

የስክሪን ግጽታቸው የተሻለ ብርሃን አለው። የባትሪ አገልግሎት ከዚህ ቀደም ከነበሩት አይፎን ስልኮች በ2.5 ሰዓት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም አይፎን 13 ስልኮች በሮዝ፣ በሰማያዊ እና በቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።

13 ስልኮች በሮዝ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።
የምስሉ መግለጫ,13 ስልኮች ከተለመዱት በተጨማሪ በሮዝ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማት አሸብረቀው መጥተዋል።

አዳዲሶቹ አይፎኖች ሚሞሪ መጠንም ወደ 500 ጊጋ ባይት ከፍ ብሏል። በአይፎን-12 ምርቶች ውስጥ ዝቀተኛ ሚሞሪ 64 ጊጋ ባይነት ነበር። አይፎን-13 ግን ዝቅተኛ የመያዝ አቅሙ ወደ 128 ጊጋ ባይት ከፍ እንዲል ሆኗል።

አፕል ብዙ ደክሞ የተለያየ ‘ፊቸር’ ያላቸውን ስልኮች ይፋ ከሚያደርግባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የቀደመውን አይፎን ስልክ የያዙ ደንበኞቹ በአዳዲስ ሞዴሎች እንዲተኳቸው ለማበረታታት እንደሆነ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ የኢንቨስትመንት ተቋሙ ዌብቡሽ እንደሚለው በመላው ዓለም የሚገኙ የአፕል ምርት የሆኑ ስልኮችን የያዙ 250 ሚሊዮን ሰዎች ባለፉት 3.5 ዓመታት ስልካቸውን በአዲስ አይፎን ሞዴል አልቀየሩም።

Presentational grey line

ዋጋ

አይፎን 13 ሚኒ ከ938 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ከ1076 ዶላር ጀምሮ፣ አይፎን 13 ፕሮ ከ1312 ዶላር ጀምሮ እንዲሁም አይፎን 13 ፕሮ ማክስ 1450 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

እያንዳንዱ አይፎን 13 ስልክ እንደ ሚሞሪ መጠኑ ዋጋው ይለያያል።

Presentational grey line

አፕል ዎች 7 እና አይፓድ

Apple watch series 7

አፕል ከስልክ በተጨማሪ ተሻሽሎ የቀረበውን አዲሱን አፕል ዎች አስተዋውቋል።

አዲሱ አፕል ዎች 7 የገዘፈ ስክሪኑ ላይ ኪቦርድ ተግጥሞለታል። አቧራ መቋቋም ይችላልም ተብሏል።

የአፕል ኩባንያ አለቃ ቲም ኩክ አዲሶቹን የአፕል አይፓዶች ሲያስተዋውቁ፤ የአይፓድ ሽያጫቸው ባለፈው ዓመት 40 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማስተማር መገደዳቸው የአይፓድ ተፈላጊነትን ጨምሮታል።

አዲሶቹ አይፓዶች ከዚህ ቀደም ከነበሩት የአፕል አይፓዶች 20 በመቶ የፈጠኑ ይሆናሉ ብለዋል።

Four iPads

የአፕል አይፓዶች ከ329 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ለገበያ ቀርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በርካታ ስማርት ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ የደቡብ ኮሪያው ሳምንስንግ መሪነቱን እንደያዛ ነው። አፕል ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።

የቻይና ኩባንያ የሚያመርታቸው ዢዮሚ ስልኮች በገበያ ደርሻ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ኦፖ እና ቪቮ የተሰኙት ስልኮች ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

Previous Articleሱዳን ውስጥ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከ80 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
Next Article በኢትዮጵያ በሁለት ቀናት ውስጥ ከ70 በላይ ሰዎች በኮቪድ መሞታቸው ተመዘገበ

Related Posts

የኑሮ ውድነት ያላቆመው የቁርጥ ሥጋ ፍቅር

September 16, 2021

በ149 ደቂቃዎች ዓለምን የቀየረው የመስከረም 1ዱ የሽብር ጥቃት ምን ይመስል ነበር?

September 16, 2021

የፀጥታው ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ መግለጫና የኢትዮጵያ አቋም

September 16, 2021

የአዲስ አበባ የ60ዎቹ የኪነ ህንፃ መለያዎች ‘እድሳት’ እና ያስነሳው ጥያቄ

September 16, 2021
Add A Comment

Leave A Reply Cancel Reply

ኣዳዲስ

የኑሮ ውድነት ያላቆመው የቁርጥ ሥጋ ፍቅር

September 16, 2021

በ149 ደቂቃዎች ዓለምን የቀየረው የመስከረም 1ዱ የሽብር ጥቃት ምን ይመስል ነበር?

September 16, 2021

የፀጥታው ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ መግለጫና የኢትዮጵያ አቋም

September 16, 2021

የአዲስ አበባ የ60ዎቹ የኪነ ህንፃ መለያዎች ‘እድሳት’ እና ያስነሳው ጥያቄ

September 16, 2021

አትራኖስ ሚድያ በዋናነት ኢንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ በሚኖሩ ባለሞያዎችና የኮሚኒቲ አባሎች ተነሳሽነትና ድጋፍ የተመሰረት በመሆኑ ዋና መስሪያ-ቤቱ ለንደን ከተማ ሲሆን በእንግሊዝ አገር ሕግ መሰረት ህጋዊ ሰዉነት ኖሮት በUK መንግስት የሚታወቅና ካምፓኒ ሃዉስ ዉስጥ የተመዘገበ ነዉ።

ተጨማሪ ገጾች
  • ስለ እኛ ለማወቅ
  • እኛን ለማግኘት
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • ማህደር
  • LIVE
ይከተሉን

መተግበርያችን ይጠቀሙ
© 2023 አትራኖስ ሚድያ

Type above and press Enter to search. Press Esc to cancel.