• ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ወቅታዊ ጉዳዮች
  • ቪድዮና ድምጾች
  • መጣጥፎች
  • ማህደር
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • LIVE
  • Language
    • ትግርኛ
    • English
አትራኖስ ሚድያ
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ወቅታዊ ጉዳዮች
  • ቪድዮና ድምጾች
  • መጣጥፎች
  • ማህደር
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • LIVE
  • Language
    • ትግርኛ
    • English
አትራኖስ ሚድያ
Home » ሱዳን ውስጥ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከ80 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
መጣጥፍ

ሱዳን ውስጥ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከ80 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

July 3, 2021Updated:September 16, 2021No Comments2 Mins Read

ባለፉት ሁለት ወራት ሱዳን ውስጥ በተከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች ከ80 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና በርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ይህ በአገሪቱ ውስጥ በጎርፍ ምክንያት በሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰው የክረምቱ ወር ከጀመረበት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ሲሆን በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አድርሷል።

የሱዳን ብሔራዊ የአደጋ መከላከያ ምክር ቤት ቃል አቀባይ በተከታታይ ወራት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ያሰከተለውን ጉዳት በተመለከተ በሰጡት መግለጫ በአጠቃላይ 84 ሰዎች መሞታቸውንና 67 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል።

ከሐምሌ ጀምሮ በአገሪቱ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ አገሪቱ ካሏት 18 ግዛቶች መካከል ቢያንስ በ14ቱ ውስጥ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

  • “የአማራ ብቻ ሳይሆን የጋምቤላ፣ የሲዳማና ደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ ገብተዋል”
  • በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ላይ ስለኢትዮጵያ ምን ተባለ?
  • ጦርነት ያፈናቀላቸው የሠሜን ወሎ እናቶችና ህጻናት ፈተና

የጎርፍ አደጋው በሰዎች ላይ ካደረሰው ጉዳት ባሻገር ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች ላይ ውድመትን ሲያደርስ፤ በማሳ ላይ የነበሩ ሰብሎች እንዲሁም መሰረተ ልማቶችም ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል።

የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ካባድ ዝናብና ጎርፍ ሱዳን ውስጥ ስላደረሰው ጉዳት ባወጣው መረጃ ላይ እንዳመለከተው፤ 102,000 የሚሆኑ ሰዎች ለችግር ተዳርገዋል።

በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምክንያት የውሃ እጥረት ሊጋጥማት እንደሚችል ስጋቷን ስትገልጽ የቆየችው ሱዳን በግዛቷ ውስጥ በሚጥለው ከባድ ዝናብና በአባይ ወንዝ አማካይነት በሚመጣው ጎርፍ ምክንያት ችግር እያጋጠማት ነው።

ባለፈው ዓመት አገሪቱ ባጋጠማት ከባድ የጎርፍ አደጋ 100 ሰዎች ሲሞቱ ከ100,000 በላይ ቤቶች ወድመውባት ከ600,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ለችግር ተጋልጠው ነበር።

በዚህም ሳቢያ ለሦስት ወራት የቆየ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋ በአደጋው የተጎዱ ዜጓቿን ለመርዳት ጥረት ስታደርግ እንደነበር ይታወሳል።

Previous Articleግድቡ በቀጣይ ወራት በሁለት ተርባይኖች እስከ 750 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል ተባለ
Next Article አፕል የረቀቁ የተባሉትን አይፎን 13 ስልኮችን አስተዋወቀ

Related Posts

የኑሮ ውድነት ያላቆመው የቁርጥ ሥጋ ፍቅር

September 16, 2021

በ149 ደቂቃዎች ዓለምን የቀየረው የመስከረም 1ዱ የሽብር ጥቃት ምን ይመስል ነበር?

September 16, 2021

የፀጥታው ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ መግለጫና የኢትዮጵያ አቋም

September 16, 2021

የአዲስ አበባ የ60ዎቹ የኪነ ህንፃ መለያዎች ‘እድሳት’ እና ያስነሳው ጥያቄ

September 16, 2021
Add A Comment

Leave A Reply Cancel Reply

ኣዳዲስ

የኑሮ ውድነት ያላቆመው የቁርጥ ሥጋ ፍቅር

September 16, 2021

በ149 ደቂቃዎች ዓለምን የቀየረው የመስከረም 1ዱ የሽብር ጥቃት ምን ይመስል ነበር?

September 16, 2021

የፀጥታው ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ መግለጫና የኢትዮጵያ አቋም

September 16, 2021

የአዲስ አበባ የ60ዎቹ የኪነ ህንፃ መለያዎች ‘እድሳት’ እና ያስነሳው ጥያቄ

September 16, 2021

አትራኖስ ሚድያ በዋናነት ኢንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ በሚኖሩ ባለሞያዎችና የኮሚኒቲ አባሎች ተነሳሽነትና ድጋፍ የተመሰረት በመሆኑ ዋና መስሪያ-ቤቱ ለንደን ከተማ ሲሆን በእንግሊዝ አገር ሕግ መሰረት ህጋዊ ሰዉነት ኖሮት በUK መንግስት የሚታወቅና ካምፓኒ ሃዉስ ዉስጥ የተመዘገበ ነዉ።

ተጨማሪ ገጾች
  • ስለ እኛ ለማወቅ
  • እኛን ለማግኘት
  • ድጋፍ ለመስጠት
  • ማህደር
  • LIVE
ይከተሉን

መተግበርያችን ይጠቀሙ
© 2023 አትራኖስ ሚድያ

Type above and press Enter to search. Press Esc to cancel.